ዮሐንስ 6:21-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. እነርሱም እንዲሳፈር ፈለጉ፤ ጀልባዋም ወዲያውኑ ወደሚሄዱበት ዳርቻ ደረሰች።

22. በማግሥቱ በባሕሩ ማዶ የቀሩት ሰዎች በዚያ አንዲት ጀልባ ብቻ እንደ ነበረች ተረዱ፤ ኢየሱስ እንዳልተሳፈረና ደቀ መዛሙርቱ ብቻቸውን እንደሄዱም ዐወቁ።

23. ከዚያም በኋላ፣ ሌሎች ጀልባዎች ከጥብር ያዶስ፣ ሕዝቡ ጌታ የባረከውን እንጀራ ወደ በላበት ስፍራ መጡ።

ዮሐንስ 6