ዘፍጥረት 36:8-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ስለዚህ ኤዶም የተባለው ዔሳው መኖሪያውን በተራራማው አገር በሴይር አደረገ።

9. በሴይር ተራራማ አገር የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት፣ የዔሳው ዝርያዎች እነዚህ ናቸው፤

10. የዔሳው ልጆች ስም፦የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጅ ኤልፋዝና የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጅ ራጉኤል፤

11. የኤልፋዝ ልጆች፦ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ጎቶምና ቄኔዝ፤

ዘፍጥረት 36