ዘፍጥረት 10:4-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. የያዋን ልጆች፦ኤሊሳ፣ ተርሴስ፣ ኪቲም፣ ሮዲኢ ናቸው።

5. ከእነዚህም በየነገዳቸው፣ በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው ተከፋፍለው በባሕር ዳርና በደሴቶች፣ በየምድራቸው የሚኖሩ ሕዝቦች ወጡ።

6. የካም ልጆች፦ኩሽ፣ ምጽራይም፣ ፉጥ፣ ከነዓን ናቸው።

7. የኩሽ ልጆች፦ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማ፣ ሰበቅታ ናቸው።የራዕማ ልጆች፦ሳባ፣ ድዳን ናቸው።

8. ኩሽ የናምሩድ አባት ነበረ፤ ናምሩድም በምድር ላይ ኀያል ሰው እየሆነ ሄደ።

ዘፍጥረት 10