ዘፀአት 40:20-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. ምስክሩን ወስዶ በታቦቱ ውስጥ አስቀመጠው፤ መሎጊያዎቹንም ከታቦቱ ጋር አያያዛቸው፤ የስርየት መክደኛውንም በላዩ ላይ አደረገው።

21. ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘው ታቦቱን ወደ ማደሪያው ድንኳን አስገብቶ መከለያ መጋረጃውን ሰቀለ፤ የምስክሩንም ታቦት ጋረደው።

22. ሙሴ ጠረጴዛውን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ፣ ከማደሪያው በስተ ሰሜን ከመጋረጃው ውጭ አኖረው፤

23. እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘውም ኅብስቱን በላዩ ላይ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት አኖረ።

24. መቅረዙን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከጠረጴዛው ትይዩ ከማደሪያው ድንኳን በስተ ደቡብ በኩል አኖረው፤

ዘፀአት 40