ዘፀአት 25:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ከእነርሱ የምትቀበላቸው ስጦታዎች እነዚህ ናቸው፦ ወርቅ፣ ብርና፣ ነሐስ፣

4. ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና የበፍታ ድር ልብስ፣ የፍየል ጠጒር፣

5. ቀይ የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፣ የለፋ ቆዳ፣ የግራር ዕንጨት፣

6. የመብራት ወይራ ዘይት፣ ለቅብዓ ዘይቱና ጣፋጭ መዓዛ ላለው ዕጣን የሚሆኑ ቅመሞች፣

ዘፀአት 25