ዘፀአት 24:14-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. እርሱም ሽማግሌዎችን “ወደ እናንተ እስክንመለስ ድረስ በዚህ ቆዩ፤ አሮንና ሖር ከእናንተ ጋር ናቸው፤ ክርክር ያለው ሰው ቢኖር ወደ እነርሱ ይሂድ።” አላቸው።

15. ሙሴ ወደ ተራራ ሲወጣ ደመናው ተራራውን ሸፈነ፤

16. የእግዚአብሔርም (ያህዌ) ክብር በሲና ተራራ ላይ ወረደ፣ ደመናውም ተራራውን እስከ ስድስት ቀን ድረስ ሸፈነው፤ በሰባተኛውም ቀን እግዚአብሔር (ያህዌ) በደመናው ውስጥ ሆኖ ሙሴን ጠራው።

ዘፀአት 24