ዘፀአት 24:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ከዚያም ሙሴን “አንተና አሮን፣ ናዳብና አብድዩ ከሰባዎቹ የእስራኤል አለቆች ጋር ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ኑ፤ ከሩቅም ስገዱ አለው፤

2. ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሊቀርብ የሚችለው ሙሴ ብቻ ነው። ሌሎቹ መቅረብ የለባቸውም ሕዝቡም ከእርሱ ጋር መምጣት የለበትም።”

3. ሙሴ ወደ ሕዝቡ ሄዶ የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ቃሎችና ሕጎች ሁሉ በነገራቸው ጊዜ በአንድ ድምፅ ሆነው፣ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ያለውን ሁሉ እናደርጋለን” አሉ።

ዘፀአት 24