18. መልካም እንዲሆንልህና እግዚአብሔር (ያህዌ) ለአባቶችህ በመሐላ እንድትወርሳት፣ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ተስፋ የሰጣቸውን መልካሚቱን ምድር ገብተህ ቀናና መልካም የሆነውን አድርግ፤
19. እግዚአብሔር (ያህዌ) በተናገረው መሠረትም ጠላቶችህን ሁሉ ከፊትህ ታስወጣለህ።
20. በሚመጡት ዘመናት ልጅህ፣ “አምላካችን እግዚአብሔር (ያህዌ ኤሎሂም) ያዘዛችሁ የመመሪያዎቹ፣ የሥርዐቶቹና የሕጎቹ ትርጒም ምንድ ነው?” ብሎ በሚጠይቅህ ጊዜ፣
21. እንዲህ በለው፤ “እኛ በግብፅ የፈርዖን ባሮች ነበርን፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) ግን በብርቱ እጅ ከግብፅ አወጣን።