ዘዳግም 33:25-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

25. የደጃፍህ መቀርቀሪያ ብረትና ናስ ይሆናል፤ኀይልህም በዘመንህ ሁሉ ይኖራል።

26. አንተን ለመርዳት በሰማያት ላይ፣በግርማው በደመናትም የሚገሠግሥ፣እንደ ይሽሩን አምላክ (ኤሎሂም) ያለ ማንም የለም።

27. ዘላለማዊ አምላክ (ኤሎሂም) መኖርያህ ነው፤የዘላለም ክንዶቹም ከሥርህ ናቸው፤‘እርሱን አጥፋው!’ በማለት፣ጠላትህን ከፊትህ ያስወግደዋል።

ዘዳግም 33