ዘዳግም 29:7-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ወደዚህ ስፍራ በደረሳችሁ ጊዜ፣ የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎንና የባሳን ንጉሥ ዐግ ሊወጉን መጡ፤ ሆኖም ድል አደረግናቸው።

8. ምድራቸውንም ወስደን፤ ለሮቤላውያን፣ ለጋዳውያንና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገን ሰጠን።

9. እንግዲህ የምታደርጉት ሁሉ እንዲከናወ ንላችሁ፣ የዚህን ኪዳን ቃሎች በጥንቃቄ ተከተሉ።

ዘዳግም 29