ዘዳግም 27:6-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. የአምላክህን የእግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) መሠዊያ ካልተጠረበ ድንጋይ ሥራ፤ በላዩም ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርብበት።

7. በዚያም የኅብረት መሥዋዕት ሠዋ፤ ብላም፣ በአምላክህ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፊት ደስ ይበልህ።

8. በድንጋዮቹ ላይ የዚህን ሕግ ቃላት ሁሉ ግልጽ አድርገህ ጻፍባቸው።”

ዘዳግም 27