ዘካርያስ 4:12-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. እንደ ገናም፣ “በሁለቱ የወርቅ ቧንቧዎች አጠገብ የወርቅ ዘይት የሚያፈሱት እነዚህ ሁለት የወይራ ቅርንጫፎች ምንድን ናቸው?” አልሁት።

13. እርሱም፣ “ምን እንደሆኑ አታውቅምን?” አለኝ።እኔም፣ “ጌታዬ ሆይ፤ አላውቅም” አልሁት።

14. እርሱም፣ “እነዚህ ሁለቱ የምድርን ሁሉ ጌታ ለማገልገል የተቀቡ ናቸው” አለኝ።

ዘካርያስ 4