ዘኁልቍ 26:52-55 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

52. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤

53. “ምድሪቱ በስማቸው ቍጥር ልክ ተደልድላ በርስትነት ለእነርሱ ትሰጥ።

54. በርከት ያለ ቊጥር ላለው ጐሣ ሰፋ ያለውን ርስት፣ አነስ ያለ ቊጥር ላለው ጐሣ ደግሞ አነስ ያለውን ስጥ፤ ርስቱንም እያንዳንዱ በዝርዝሩ ላይ በተመለከተው ቊጥር መሠረት ይረከባል።

55. የመሬት ድል ድሉም በዕጣ ይሁን፤ እያንዳንዱ የሚወርሰውም በየነገድ አባቶቹ ስም ይሆናል።

ዘኁልቍ 26