ዘኁልቍ 26:43-46 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

43. ሁሉም የሰምዔያውያን ጐሣዎች ነበሩ፤ ከእነዚህ የተቈጠሩት ደግሞ ሥልሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።

44. የአሴር ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤በዩምና በኩል፣ የዩምናውያን ጐሣ፣በየሱዋ በኩል፣ የየሱዋውያን ጐሣ፣በበሪዓ በኩል፣ የበሪዓውያን ጐሣ፤

45. እንዲሁም በበሪዓ ዘሮች በኩል፣በሔቤር በኩል፣ የሔቤራውያን ጐሣ፣በመልኪኤል በኩል፣ የመልኪኤላውያን ጐሣ።

46. አሴር ሤራሕ የምትባል ልጅ ነበረችው።

ዘኁልቍ 26