9. ሆኖም በመቅሠፍቱ የሞተው ሰው ቍጥር ሃያ አራት ሺህ ደርሶ ነበር።
10. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤
11. “የካህኑ የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ እኔ ለክብሬ በመካከላቸው እንደ ምቀና ስለ ቀና ቍጣዬን ከእስራኤላውያን መልሶታል፤ ስለዚህ እኔም በቅናቴ ጨርሶ አላጠፋኋቸውም፤
12. ስለዚህ እነሆ እኔ የሰላም ቃል ኪዳኔን ከእርሱ ጋር እንደማደርግ ንገረው።
13. ለአምላኩ (ኤሎሂም) ክብር ቀንቶ ለእስራኤላውያን ስላስተሰረየላቸው፣ እርሱና ልጆቹ ዘላቂ የክህነት ቃል ኪዳን ይኖራቸዋል።