ዘኁልቍ 15:4-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. መሥዋዕቱን ይዞ የሚመጣው ሰው በኢን አንድ አራተኛ ዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ ዐሥረኛ የላመ ዱቄት የእህል ቊርባን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ያቀርባል።

5. ለሚቃጠል ወይም ለዕርድ መሥዋዕት ከሚቀርብ ከእያንዳንዱ የበግ ጠቦት ጋር የኢን አንድ አራተኛ የወይን ጠጅ የመጠጥ ቊርባን አብራችሁ አዘጋጁ።

6. “ ‘ከአውራ በግ ጋር በኢን ሢሶ ዘይት የተለወሰ የኢፍ ሁለት ዐሥረኛ ልም ዱቄት የእህል ቍርባን አዘጋጁ፤

7. እንዲሁም ለመጠጥ ቊርባን የሚሆን የኢን አንድ ሦስተኛ የወይን ጠጅ አዘጋጁ፤ ይህንም እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ ሽታ ያለው አድርጋችሁ አቅርቡ።

ዘኁልቍ 15