ዘሌዋውያን 7:17-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. እስከ ሦስት ቀን የቆየ ማንኛውም የመሥዋዕቱ ሥጋ ይቃጠል።

18. ማንኛውም የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ በሦስተኛው ቀን ከተበላ ተቀባይነት የለውም፤ ርኵስ በመሆኑ ላቀረበው ሰው ዋጋ አይኖረውም፤ ከዚያም የበላ ሰው የበደል ዕዳ ይሆንበታል።

19. “ ‘ርኩስ ከሆነ ነገር ጋር የተነካካ ሥጋ ይቃጠል እንጂ አይበላ። ሌላውን ሥጋ ግን በሥርዐቱ መሠረት ንጹሕ የሆነ ማንኛውም ሰው ይብላ፤

20. ነገር ግን ንጹሕ ያልሆነ ማንኛውም ሰው ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የቀረበውን የትኛውንም የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፣ ከሕዝቡ ፈጽሞ ይወገድ።

ዘሌዋውያን 7