ዕንባቆም 1:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ነቢዩ ዕንባቆም የተቀበለው ንግር፤

2. እግዚአብሔር ሆይ፤ ለርዳታ እየተጣራሁ፣አንተ የማትሰማው እስከ መቼ ነው?“ግፍ በዛ” ብዬ እየጮኽሁ፣አንተ የማታድነው እስከ መቼ ነው?

3. ስለ ምን በደልን እንዳይ አደረግኸኝ?እንዴትስ ግፍ ሲፈጸም ትታገሣለህ?ጥፋትና ግፍ በፊቴ አለ፤ጠብና ግጭት በዝቶአል።

ዕንባቆም 1