ኤርምያስ 8:9-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ጥበበኞች ያፍራሉ፤ይዋረዳሉ፤ በወጥመድም ይያዛሉ። የእግዚአብሔርን ቃል ተቃውመው፣ምን ዐይነት ጥበብ ይኖራቸዋል?

10. ስለዚህ ሚስቶቻቸውንም ለሌሎች ወንዶች እሰጣለሁ፤ዕርሻዎቻቸውንም ለባዕዳን እሰጣለሁ፤ከታናሹ እስከ ታላቁ ድረስ፣ሁሉም ተገቢ ላልሆነ ጥቅም ይስገበገባሉ፤ነቢያትና ካህናትም እንዲሁ፤ሁሉም ያጭበረብራሉ።

11. የሕዝቤን ቍስል ብርቱ እንዳይደለ በመቍጠር፣የተሟላ ፈውስ ሳይኖር እንዲሁ ያክማሉ፤ሰላም ሳይኖር፣“ሰላም፣ ሰላም” ይላሉ።

12. ርኵሰት ሲፈጽሙ ዐፍረው ነበርን?የለም! በጭራሽ አላፈሩም፤ኀፍረት ምን እንደሆነም አያውቁም።ስለዚህ ከወደቁት ጋር ይወድቃሉ፤በምቀጣቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፤”ይላል እግዚአብሔር።

ኤርምያስ 8