ኤርምያስ 8:12-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. ርኵሰት ሲፈጽሙ ዐፍረው ነበርን?የለም! በጭራሽ አላፈሩም፤ኀፍረት ምን እንደሆነም አያውቁም።ስለዚህ ከወደቁት ጋር ይወድቃሉ፤በምቀጣቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፤”ይላል እግዚአብሔር።

13. “ ‘ያመረቱትን ሁሉ እወስድባቸዋለሁ፤ይላል እግዚአብሔር፤በወይን ተክል ላይ የወይን ፍሬ አይኖርም፤በበለስ ዛፍ ላይ የበለስ ፍሬ አይገኝም፤ቅጠሎቻቸውም ይረግፋሉ።የሰጠኋቸው በሙሉ፣ከእነርሱ ይወሰድባቸዋል።’ ”

14. “ለምን እዚህ እንቀመጣለን?በአንድነት ተሰብሰቡ!ወደ ተመሸጉት ከተሞች እንሽሽ፤በዚያም እንጥፋ!በእርሱ ላይ ኀጢአትን ስላደረግን፣ እግዚአብሔር አምላካችን እንድንጠፋ አድርጎናል፤የተመረዘ ውሃ እንድንጠጣ ሰጥቶናል።

15. ሰላምን ተስፋ አደረግን፤መልካም ነገር ግን አልመጣም፤የፈውስ ጊዜን ተመኘን፤ነገር ግን ሽብር ብቻ ሆነብን።

16. የጠላት ፈረሶች ፉርፉርታ፣ከዳን ይሰማል፤በድንጒላ ፈረሶቻቸው ማሽካካት፣መላዋ ምድር ተንቀጠቀጠች።ምድሪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ፣ከተማዪቱንና በውስጧ የሚኖሩትን ሁሉ፣ሊውጡ መጡ።”

ኤርምያስ 8