ኤርምያስ 51:55-58 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

55. እግዚአብሔር ባቢሎንን ያጠፋታል፤ታላቅ ጩኸቷንም ጸጥ ያደርጋል።ሞገዳቸው እንደ ታላቅ ውሃ ይተማል፤ጩኸታቸውም ያስተጋባል።

56. በባቢሎን ላይ አጥፊ ይመጣል፤ጦረኞቿ ይማረካሉ፤ቀስታቸውም ይሰበራል፤ እግዚአብሔር ግፍን የሚበቀል፣ተገቢውንም ሁሉ የሚከፍል አምላክ ነውና።

57. ባለ ሥልጣኖቿንና ጥበበኞቿን፣ገዦቿንና መኳንንቷን፣ ጦረኞቿንም አሰክራለሁ፤ለዘላለም ይተኛሉ፤ አይነቁምም፤”ይላል ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነው ንጉሥ።

58. የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ወፍራሙ የባቢሎን ቅጥር ፈጽሞ ይፈርሳል፤ከፍ ያሉት ደጆቿም በእሳት ይቃጠላሉ፤ሰዎቹ በከንቱ ይደክማሉ፤የሕዝቡም ልፋት ለእሳት ይሆናል።”

ኤርምያስ 51