ኤርምያስ 51:4-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. በባቢሎን ምድር ታርደው፣በአደባባዮቿም እስከ ሞት ቈስለው ይወድቃሉ።

5. ምድራቸው በእስራኤል ቅዱስ ፊት፣በበደል የተሞላች ብትሆንም፣እስራኤልንና ይሁዳን አምላካቸው፣የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር አልጣላቸውም።

6. “ከባቢሎን ሸሽታችሁ ውጡፈጥናችሁም ሕይወታችሁን አትርፉ!በኀጢአቷ ምክንያት አትጥፉ። የእግዚአብሔር የበቀል ጊዜ ነው፤እርሱም የሥራዋን ይከፍላታል።

ኤርምያስ 51