ኤርምያስ 51:3-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ቀስተኛው ቀስቱን እስኪገትር፣የጦር ልብሱንም እስኪለብስ ፋታ አትስጡት፤ለወጣቶቿ አትዘኑ፤ሰራዊቷንም ፈጽማችሁ አጥፉ።

4. በባቢሎን ምድር ታርደው፣በአደባባዮቿም እስከ ሞት ቈስለው ይወድቃሉ።

5. ምድራቸው በእስራኤል ቅዱስ ፊት፣በበደል የተሞላች ብትሆንም፣እስራኤልንና ይሁዳን አምላካቸው፣የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር አልጣላቸውም።

6. “ከባቢሎን ሸሽታችሁ ውጡፈጥናችሁም ሕይወታችሁን አትርፉ!በኀጢአቷ ምክንያት አትጥፉ። የእግዚአብሔር የበቀል ጊዜ ነው፤እርሱም የሥራዋን ይከፍላታል።

7. ባቢሎን በእግዚአብሔር እጅ የወርቅ ጽዋ ነበረች፤ምድርንም ሁሉ አሰከረች።ሕዝቦች ከወይን ጠጇ ጠጡ፤ስለዚህ አሁን አብደዋል።

ኤርምያስ 51