ኤርምያስ 5:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “በኢየሩሳሌም መንገዶች እስቲ ውጡ፤ ወደ ላይ ወደታችም ውረዱ፤ዙሪያውን ተመልከቱ ቃኙ፤በአደባባይዋም ፈልጉ፤እውነትን የሚሻና በቅንነት የሚሄድ፣አንድ ሰው እንኳ ብታገኙ፣እኔ ይህቺን ከተማ እምራታለሁ።

2. ‘ሕያው እግዚአብሔርን! ቢሉም፣የሚምሉት በሐሰት ነው።”

3. እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐይኖችህ እውነትን አይመለከቱምን?አንተ መታሃቸው፤ እነርሱ ግን አልተሰማቸውም፤አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ግን አልታረሙም፤ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠነከሩበንስሓ ለመመለስም አልፈለጉም።

ኤርምያስ 5