ኤርምያስ 49:37-39 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

37. ነፍሳቸውን በሚሹ ጠላቶቻቸው ፊት፣ኤላምን አርበደብዳለሁ፤በላያቸው ላይ መዓትን፣ይኸውም ቍጣዬን አመጣባቸዋለሁ፤”ይላል እግዚአብሔር፤“ፈጽሜ አስካጠፋቸውም ድረስ፣በሰይፍ አሳድዳቸዋለሁ።

38. ዙፋኔን በኤላም እዘረጋለሁ፤ነገሥታቷንና መኳንንቷን አጠፋለሁ፤”ይላል እግዚአብሔር፤

39. “ነገር ግን የኋላ ኋላ፣የኤላምን ምርኮ እመልሳለሁ፤”ይላል እግዚአብሔር።

ኤርምያስ 49