ኤርምያስ 49:23-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. ስለ ደማስቆ፤“ክፉ ወሬ ሰምተዋልና፣ሐማትና አርፋድ ደንግጠዋል፤እንደ ተናወጠ ባሕርም ታውከዋል፤ልባቸውም ቀልጦአል።

24. ደማስቆ ተዳከመች፤ትሸሽም ዘንድ ወደ ኋላ ተመለሰች፤ብርክ ያዛት፣ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ጭንቅና መከራ ዋጣት።

25. ደስ የምሰኝባት፣የታወቀችው ከተማ እንዴት ተተወች?

26. በርግጥ ወንዶች ወጣቶቿ በየአደባባዩ ይረግፋሉ፤በዚያ ቀን ወታደሮቿ ሁሉ ይወድቃሉ፤”ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤

27. “በደማስቆ ቅጥር ላይ እሳት እለኵሳለሁ፤የወልደ አዴርንም ዐምባ ይበላል።”

ኤርምያስ 49