ኤርምያስ 48:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ስለ ሞዓብ፤የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ናባው ትጠፋለችና ወዮላት፤ቂርያታይም ትዋረዳለች፤ ትያዛለችም፤ምሽጎች ይደፈራሉ፤ ይፈራርሳሉም።

2. ከእንግዲህ ሞዓብ አትከበርም፤ሰዎች በሐሴቦን ተቀምጠው፣‘ኑ ያቺን አገር እናጥፋት’ ብለው ይዶልቱባታል።መድሜን ሆይ፤ አንቺም ደግሞ ጸጥ ትደረጊያለሽ፤ሰይፍም ያሳድድሻል።

3. ከሖሮናይም የሚወጣውን ጩኸት፣የመውደምና የታላቅ ጥፋት ድምፅ ስሙ!

4. ሞዓብ ትሰበራለች፤ልጆቿም ጩኸት ያሰማሉ።

ኤርምያስ 48