ኤርምያስ 4:12-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. በእኔ ትእዛዝ ይነፍሳል፤ እንግዲህ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ።”

13. እነሆ፤ እንደ ደመና ይንሰራፋል፤ሠረገሎቹ እንደ ዐውሎ ነፋስ ይመጣሉ፤ፈረሶቹም ከንስር ይፈጥናሉ፤መጥፋታችን ነውና ወዮልን!

14. ኢየሩሳሌም ሆይ፤ እንድትድኚ ከልብሽ ክፋት ታጠቢ፤እስከ መቼ ክፉ ሐሳብ በውስጥሽ ይኖራል?

15. ድምፅ ከዳን ይሰማልና፤ከኤፍሬም ተራሮችም ጥፋትን ያውጃል።

ኤርምያስ 4