ኤርምያስ 20:5-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. የዚህችን ከተማ ሀብት ሁሉ፣ ጥሪቷን፣ የይሁዳን ነገሥታት ውድ ዕቃና ንብረት ሁሉ ለጠላቶቻቸው አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እነርሱም ዘርፈው ወደ ባቢሎን ይዘውት ይሄዳሉ።

6. ጳስኮር ሆይ፤ አንተና በቤትህ የሚኖሩት ሁሉ ወደ ባቢሎን ትጋዛላችሁ። አንተና በሐሰት ትንቢት የተነበይህላቸው ባልንጆሮችህ በዚያ ትሞታላችሁ፤ በዚያም ትቀበራላችሁ።’ ”

7. እግዚአብሔር ሆይ፤ አታለልኸኝ፤ እኔም ተታለልሁ፤አንተ ከእኔ እጅግ በረታህ፤ አሸነፍህም፤ቀኑን ሙሉ ማላገጫ ሆንሁ፤ሁሉም ተዘባበቱብኝ።

ኤርምያስ 20