ኤርምያስ 13:22-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. “ይህ ለምን ደረሰብኝ?” ብለሽራስሽን ብትጠይቂ፣ልብስሽን ተገልበሽ የተገፈተርሽው፣በሰውም እጅ የተንገላታሽው፣ከኀጢአትሽ ብዛት የተነሣ ነው።

23. ኢትዮጵያዊ መልኩን፣ነብርስ ዝንጒርጒርነቱን መለወጥ ይችላልን?እናንት ክፉ ማድረግ የለመዳችሁትም፣መልካም ማድረግ አትችሉም።

24. “የበረሓ ነፋስ ብትንትኑን እንደሚያወጣው ገለባ፣እንዲሁ እበታትናችኋለሁ።

25. እኔን ረስተሽ፣በከንቱ አማልክት ስለታመንሽ፣ያወጅሁልሽ ድርሻሽ፣ዕጣ ፈንታሽ ይህ ነው፤”ይላል እግዚአብሔር፤

26. “ኀፍረትሽ እንዲገለጥ፣ልብስሽን ፊትሽ ድረስ እገልባለሁ፤

ኤርምያስ 13