ኤርምያስ 10:23-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. እግዚአብሔር ሆይ፤ የሰው ሕይወት በራሱ እጅ እንዳልሆነች፣አካሄዱንም በራሱ አቃንቶ ሊመራእንደማይችል ዐውቃለሁ።

24. እግዚአብሔር ሆይ፤ ቅጣኝ፤ ብቻ በመጠኑ ይሁንልኝ፤ፈጽሞ እንዳልጠፋ፣በቍጣህ አትምጣብኝ።

25. ያዕቆብን አሟጠው ስለበሉት፣ፈጽመው ስለዋጡት፣መኖሪያውንም ወና ስላደረጉ፣በማያውቁህ ሕዝቦች፣ስምህንም በማይጠሩ ወገኖች ላይ፣ቍጣህን አፍስስ።

ኤርምያስ 10