ኢዮብ 9:27-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. ‘ማጒረምረሜን እረሳለሁ፤ገጽታዬን ቀይሬ ፈገግ እላለሁ’ ብል፣

28. ንጹሕ አድርገህ እንደማትቈጥረኝ ስለማውቅ፣መከራዬን ሁሉ እፈራለሁ።

29. በደለኛ መሆኔ ካልቀረ፣ለምን በከንቱ እለፋለሁ?

30. ሰውነቴን በሳሙና ብታጠብ፣እጄንም በልዩ መታጠቢያ ባነጻ፣

31. ልብሴ እንኳ እስኪጸየፈኝ ድረስ፣በዐዘቅት ውስጥ ታሰጥመኛለህ።

ኢዮብ 9