ኢዮብ 8:9-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. እኛ ትናንት ስለ ተወለድን አንዳች አናውቅምና፤ዘመናችንም በምድር ላይ እንደ ጥላ ነው።

10. እነርሱ የሚያስተምሩህና የሚነግሩህ፣ከልቦናቸውም ቃልን የሚያወጡ አይደሉምን?

11. ደንገል ረግረግ በሌለበት ስፍራ ይበቅላልን?ቄጠማስ ውሃ በሌለበት ይለመልማልን?

12. ገና በማደግ ላይ እያለ ሳይታጨድ፣ከሌሎች ዕፀዋት ፈጥኖ ይደርቃል።

ኢዮብ 8