ኢዮብ 5:14-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ቀኑ ጨለማ ይሆንባቸዋል፤በቀትርም ጊዜ በሌሊት እንዳለ ሰው በዳበሳ ይሄዳሉ።

15. ችግረኛውን ከአፋቸው ሰይፍ፣ከኀይለኛውም እጅ ያድነዋል።

16. ስለዚህ ድኻ ተስፋ አለው፤ዐመፅም አፏን ትዘጋለች።

17. “እነሆ፤ እግዚአብሔር የሚገሥጸው ሰው ምስጉን ነው፤ስለዚህ ሁሉን የሚችለውን አምላክ ተግሣጽ አትናቅ።

ኢዮብ 5