ኢዮብ 42:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ኢዮብም እንዲህ ሲል ለእግዚአብሔር መለሰ፤

2. “አንተ ሁሉን ማድረግ እንደምትችል፣ዕቅድህም ከቶ እንደማይሰናከል ዐወቅሁ።

3. አንተ፣ ‘ያለ ዕውቀት ዕቅዴን የሚያደበዝዝ ይህ ማን ነው’ አልኸኝ፤በእርግጥ ያልገባኝን ነገር፣የማላውቀውንና ላስተውለው የማልችለውን ጒዳይ ተናገርሁ።

4. “ ‘ስማኝ፣ ልናገር እኔ እጠይቃለሁ፤አንተ ትመልስልኛለህ’ አልኸኝ።

ኢዮብ 42