ኢዮብ 41:26-30 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

26. ጦር፣ ፍላጻ ወይም አንካሴ፣ሰይፍም ቢያገኘው አንዳች አይጐዳውም።

27. እርሱ ብረትን እንደ አገዳ፣ናስንም እንደ ነቀዘ ዕንጨት ይቈጥራል።

28. ቀስት አያባርረውም፤የወንጭፍ ድንጋይም ለእርሱ እንደ ገለባ ነው።

29. ቈመጥ በእርሱ ፊት እንደ ገለባ ነው፤ጦር ሲሰበቅ ይሥቃል።

30. የሆዱ ሥር እንደ ሸካራ ገል ነው፤እንደ መውቂያ መሣሪያም በጭቃ ላይ ምልክት ጥሎ ያልፋል።

ኢዮብ 41