ኢዮብ 40:6-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. እግዚአብሔርም በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ፣ ለኢዮብ እንዲህ ሲል ተናገረ፤

7. “እንግዲህ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤እኔ እጠይቅሃለሁ፤አንተም መልስልኝ።

8. “ፍርዴን ታቃልላለህን?ወይስ አንተ ጻድቅ ለመሆን እኔን ትኰንናለህ?

9. እንደ እግዚአብሔር ክንድ ያለ ክንድ አለህን?ድምፅህስ እንደ እርሱ ድምፅ ሊያንጐደጒድ ይችላልን?

ኢዮብ 40