ኢዮብ 4:11-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ብርቱው አንበሳ አደን በማጣት ይሞታል፤የአንበሳዪቱም ግልገሎች ይበተናሉ።

12. “ቃል በምስጢር መጣልኝ፤ጆሮዬም ሹክሹክታውን ሰማች።

13. በሚያስጨንቅ የሌሊት ሕልም ውስጥ፣ከባድ እንቅልፍም በሰዎች ላይ በወደቀ ጊዜ፣

14. ፍርሀትና መንቀጥቀጥ ያዘኝ፤ዐጥንቶቼም ሁሉ ተናወጡ።

15. መንፈስ ሽው ብሎ በፊቴ አለፈ፤የገላዬም ጠጒር ቆመ።

ኢዮብ 4