ኢዮብ 4:10-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. አንበሳ ያገሣል፤ ቍጡውም አንበሳ ይጮኻል፤የደቦል አንበሳው ጥርስ ግን ተሰብሮአል።

11. ብርቱው አንበሳ አደን በማጣት ይሞታል፤የአንበሳዪቱም ግልገሎች ይበተናሉ።

12. “ቃል በምስጢር መጣልኝ፤ጆሮዬም ሹክሹክታውን ሰማች።

13. በሚያስጨንቅ የሌሊት ሕልም ውስጥ፣ከባድ እንቅልፍም በሰዎች ላይ በወደቀ ጊዜ፣

14. ፍርሀትና መንቀጥቀጥ ያዘኝ፤ዐጥንቶቼም ሁሉ ተናወጡ።

15. መንፈስ ሽው ብሎ በፊቴ አለፈ፤የገላዬም ጠጒር ቆመ።

ኢዮብ 4