ኢዮብ 38:24-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

24. መብረቅ ወደሚሰራጭበት ቦታ የሚያደርሰው መንገድ፣የምሥራቅም ነፋስ በምድር ላይ ወደሚበተንበት ስፍራ የሚወስደው የትኛው ነው?

25. ለዝናብ መውረጃን፣ለመብረቅም መንገድን ያበጀ ማን ነው?

26. በዚህም ማንም የማይኖርበትን ምድር፣ሰውም የሌለበትን ምድረ በዳ የሚያጠጣ፣

27. ባድማውንና በረሓውን መሬት የሚያጠግብ፣ሣርም እንዲበቅልበት የሚያደርግ ማን ነው?

28. ዝናብ አባት አለውን?የጤዛን ጠብታ ማን ወለደው?

ኢዮብ 38