ኢዮብ 36:8-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ነገር ግን ሰዎች በሰንሰለት ቢታሰሩ፣በመከራም ገመድ ቢጠፈሩ፣

9. በእብሪት የፈጸሙትን በደል፣ተግባራቸውን ይነግራቸዋል።

10. ተግሣጽን እንዲሰሙ ያደርጋቸዋል፤ከክፋታቸውም እንዲመለሱ ያዛቸዋል።

11. ታዘው ቢያገለግሉት፣ቀሪ ዘመናቸውን በተድላ፣ዕድሜያቸውንም በርካታ ይፈጽማሉ።

12. ባይሰሙ ግን፣በሰይፍ ይጠፋሉ፤ያለ ዕውቀትም ይሞታሉ።

ኢዮብ 36