ኢዮብ 36:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ዕውቀቴን ከሩቅ አመጣለሁ፤ፈጣሪዬ ጻድቅ እንደሆነ እገልጻለሁ።

4. ቃሌ ሐሰት እንዳልሆነ አረጋግጣለሁ፤በዕውቀቱ ፍጹም የሆነ ሰው ከአንተ ጋር ነው።

5. “እግዚአብሔር ኀያል ነው፤ ግን ማንንም አይንቅም፤ኀያል፣ በዐላማውም ጽኑ ነው።

6. ክፉዎችን በሕይወት አያኖርም፤ለተቸገሩት ግን በቅን ይፈርዳል።

ኢዮብ 36