ኢዮብ 33:4-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጥሮኛል፤ሁሉን የሚችለውም አምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጥቶኛል።

5. የምትችል ከሆነ መልስልኝ፤ተዘጋጅተህም በፊቴ ቁም።

6. በእግዚአብሔር ፊት እኔም እንዳንተው ነኝ፤የተፈጠርሁትም ደግሞ ከዐፈር ነው።

7. እኔን መፍራት የለብህም፤እጄም ሊከብድብህ አይገባም።

8. “በእርግጥ የተናገርኸውን ሰምቻለሁ፤እንዲህም ስትል አድምጫለሁ፤

ኢዮብ 33