ኢዮብ 31:25-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

25. እጄ ባገኘችው ሀብት፣በባለጠግነቴም ብዛት ደስ ብሎኝ ከሆነ፣

26. የፀሓይን ድምቀት አይቼ፣ወይም የጨረቃን አካሄድ ግርማ ተመልክቼ፣

27. ልቤ በስውር ተታልሎ፣ስለ ክብራቸው አፌ እጄን ስሞ ከሆነ፣

28. ለልዑል እግዚአብሔር ታማኝ አለመሆኔ ነውና፣ይህም ደግሞ የሚያስቀጣኝ በደል በሆነ ነበር።

ኢዮብ 31