ኢዮብ 31:24-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

24. “ወርቅን ተስፋ አድርጌ፣ወይም ንጹሑን ወርቅ፣ ‘አንተ መታመኛዬ ነህ’ ብዬ ከሆነ፣

25. እጄ ባገኘችው ሀብት፣በባለጠግነቴም ብዛት ደስ ብሎኝ ከሆነ፣

26. የፀሓይን ድምቀት አይቼ፣ወይም የጨረቃን አካሄድ ግርማ ተመልክቼ፣

27. ልቤ በስውር ተታልሎ፣ስለ ክብራቸው አፌ እጄን ስሞ ከሆነ፣

ኢዮብ 31