ኢዮብ 30:7-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. በጫካ ውስጥ ያናፋሉ፤በእሾሃማ ቍጥቋጦ መካከልም ይታፈጋሉ።

8. ስማቸው የማይታወቅ አልባሌ ናቸው፤ከምድሪቱም ተባረዋል።

9. “አሁን ግን ልጆቻቸው በዘፈን ይሣለቁብኛል፤በእነርሱም ዘንድ መተረቻ ሆኛለሁ።

10. ይጸየፉኛል ወደ እኔም አይቀርቡም፤ያለ ምንም ይሉኝታ በፊቴ ይተፋሉ።

11. እግዚአብሔር የቀስቴን አውታር ስላላላውና በመከራም ስለ መታኝ፣በፊቴ መቈጠብን ትተዋል።

12. በቀኜ በኩል ባለጌዎች ሆ! ብለው ተነሡብኝ፤ለእግሬም ወጥመድ ዘረጉ፤የዐፈር ድልድልም አዘጋጁብኝ።

ኢዮብ 30