ኢዮብ 30:21-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. ተመልሰህ ጨካኝ ሆንህብኝ፤በክንድህም ብርታት አስጨነቅኸኝ።

22. ወደ ላይ ነጥቀህ በነፋስ ፊት አበረርኸኝ፤በዐውሎ ነፋስም ወዲያ ወዲህ ወዘወዝኸኝ።

23. ለሕያዋን ሁሉ ወደ ተመደበው ስፍራ፣ወደ ሞት እንደምታወርደኝ ዐውቃለሁ።

24. “የተጐዳ ሰው ተጨንቆ ድረሱልኝ ብሎ ሲጮኽ፣በእርግጥ ክንዱን የሚያነሣበት ማንም የለም።

ኢዮብ 30