ኢዮብ 27:14-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ልጆቹ የቱንም ያህል ቢበዙም ለሰይፍ ይዳረጋሉ፤ዘሩም ጠግቦ አያድርም።

15. የተረፉለትም በመቅሠፍት አልቀው ይቀበራሉ፤መበለቶቻቸውም አያለቅሱላቸውም።

16. ብርን እንደ ዐፈር ቢከምር፣ልብስንም እንደ ሸክላ ጭቃ ቢያከማች፣

17. እርሱ ያከማቸውን ጻድቃን ይለብሱታል፤ብሩንም ንጹሓን ይከፋፈሉታል።

18. የሚሠራው ቤት እንደ ሸረሪት ድር፣እህል ጠባቂም እንደ ቀለሰው መጠለያ ነው።

ኢዮብ 27