ኢዮብ 24:20-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. የተሸከመቻቸው ማሕፀን ትረሳቸዋለች፤ትል ይቦጠቡጣቸዋል፤ክፉዎች እንደ ዛፍ ይሰበራሉ፤የሚያስታውሳቸውም የለም።

21. የማትወልደውን መካኒቱን ይቦጠቡጣሉ፤ለመበለቲቱም አይራሩም።

22. ነገር ግን እግዚአብሔር ብርቱዎችን በኀይሉ ጐትቶ ይጥላል፤ቢደላደሉም የሕይወት ዋስትና የላቸውም።

23. ያለ ሥጋት እንዲኖሩ ትቶአቸው ይሆናል፤ዐይኖቹ ግን በመንገዳቸው ላይ ናቸው።

24. ለጥቂት ጊዜ ከፍ ከፍ ይላሉ፤ ሆኖም ይጠፋሉ፤ዝቅ ዝቅ ብለው፤ እንደ ሌሎቹ ይከማቻሉ።እንደ እህል ራስም ይታጨዳሉ።

ኢዮብ 24