ኢዮብ 22:27-30 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. ወደ እርሱ ትጸልያለህ፤ እርሱም ይሰማሃል፤አንተም ስእለትህን ትሰጣለህ።

28. ያሰብኸው ይከናወንልሃል፤በመንገድህም ላይ ብርሃን ይበራል።

29. ሰዎች ቢዋረዱና አንተ፣ ‘ከፍ አድርጋቸው’ ብትል፣እርሱ ዝቅ ያሉትን ያድናል፤

30. በጎ ያልሆነውን ሰው እንኳ፣ከአንተ እጅ ንጽሕና የተነሣ ያድነዋል።”

ኢዮብ 22